Beyond the Sea.

Ethiopian Shipping and Logistics

የጨረታ መለያ ቁጥር፡ ESL/KT/NCB/S/CR/01/18

በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ቃሊቲ ትራኪንግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በጂቡቲ ኮሪደር እና የተለያዩ የክልል መዳረሻዎች የሚያሰማራቸው ከባድ ተሽከርካሪዎች የመውደቅ/መገልበጥ አደጋ በሚያጋጥማቸው ወቅት የወደቀውን ጭነት ለማስነሳት የተንቀሳቃሽ ክሬን ኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  • 1. ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣.
  • 2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ብቻ Ethiopian Shipping & Logistics Service Enterprise Kality Branch Office በሚል በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • 3. ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ስዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ቃሊቲ በሚገኘው የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ቃሊቲ ትራኪንግ ግዥ ዋና ክፍል ቀርበው የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000008631925 (Ethiopian Shipping & Logistics Service Enterprise Kality Branch Office) ገቢ በማድረግ ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  • 4. ተጫራቾች ቴክኒካልና የፋይናንሺያል “posta” ኦርጂናል እና ኮፒ “Posta” ላይ የጨረታ መለያ ቁጥር: ESL/KT/NCB/S/CR/01/18 በመፃፍ በቅ/ጽ/ቤቱ የግዥ ዋና ክፍል እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ስዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡.

  • 5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ለሚመጣው የሥራ ቀን የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
  • 6. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ETHIOPIAN SHIPPING AND LOGISTICS, KALITY TRUCKING BRANCH OFFICE
    Tell: 0911-56-96-82 / 0961-09-80-39