Beyond the Sea.

Ethiopian Shipping and Logistics

የሐራጅ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የሐራጅ ጨረታ ቁጥር ሐጅ/05/2018

በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል መጋዘን የሚገኙ የተወረሱ ንብረቶች የሐራጅ ሽያጭ

በጅቡቲ የባህር ወደብ ላይ የቆይታ ጊዜያቸው ያለፈ እና ወደ ኢትዮጲያ የተላኩ ዕቃዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በአስመጪዎቻቸው ጥቅም ላይ የሚውሉበትን ወይም የሚወገዱበት አኳኋን ለመወሰን በወጣው መመሪያ ቁጥር 33/2005 ተራ ቁጥር 4.7 ላይ እንደተመለከተው በጅቡቲ የባህር ወደብ ላይ የቆይታ ጊዜቸው ያለፈ ዕቃዎች ከጅቡቲ ወደብ ተጓጉዘው በኢትዮጲያ የጉምሩክ ክልል ወደሚገኙ ደረቅ ወደቦች ወይም ሌሎች አመቺ የማከማቻ ሥፍራዎች ከደረሱበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አስመጪዎች በዕቃዎቹ ላይ ሊከፈል የሚገባውን ቀረጥና ታክስ፤የወደብ አገልግሎት ክፍያ እንዲሁም ዕቃውን ከጅቡቲ ወደብ ለማጓጓዝ እና በደረቅ ወደቦች ወይም በሌሎች አመቺ የማከማቻ ሥፍራዎች እንዲቆዩ ለማድረግ የወጣውን ማንኛውንም ወጪ ከፍለው ዕቃዎችን እንዲረከቡ እንደሚያደርግ ነገር ግን አስመጪዎች በተሰጣቸው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚፈለግባቸውን ክፍያ ከፍለው ዕቃውን ካላነሱ እንደተተወ ዕቃዎች ተቆጥረው በሐራጅ የሽያጭ ዘዴ እንደሚሸጡ እና ሽያጩን ወይም የማስወገድሥራውን እንዲያከናውን ለድርጅታችን የኢትዮጲያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲከስ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ወቷል፡፡

ከታች በሰንጠረዥ 1 በተለያዩ ኮንቴይነር ቁጥር ከተራ ቁጥር 1 እስከ 10 የተመላከቱት ንብረቶች በንብረቶቹ ትይዩ በተናጠል እና በጥቅል በተቀመጠው የሐራጅ ጨረታ መነሻ ዋጋ መሰረት በማድረግ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ላቀረበ፤የዘመኑን ግብር ለከፈለ፤በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ ማቅረብ እና የጨረታ ማስከበሪያ 20% C.P.O የገንዘብ መጠን በንብረቶቹ ትይዩ የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በድርጅታችን ሥም በማሰራት ማቅረብ ለቻላ ተጫራች የቀረበ ነው፡፡ ተጫራች በጥቅሉ በተመላከቱት ንብረቶች ላይ መወዳደር የሚችሉት በጥቅሉ እንዲሁም በተናጠል በተመላከቱት ንብረቶች ላይ መወዳደር የሚችሉት በተናጠል በተቀመጠው መሰረት ብቻ ነው፡፡ በተራ ቁጥር 11 ላይ የተመለከተውን ተሸከርካሪ በተቀመጠው የሐራጅ ጨረታ መነሻ ዋጋ መሰረት በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ 20% C.P.O የገንዘብ መጠን በድርጅታችን ሥም በማሰራት ማቅረብ ለቻላ ማንኛውም ተጫራች የቀረበ ሲሆን ምንም አይነት ንግድ ፍቃድ አይጠይቅም፡፡

ለዠርዝር መረጃ እዚህ ጋር ይጫኑ

Click Here