TENDER NO፡ RFQ: ESLSE/P&T/NEG/2025/01859
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የወረታ ወደብና ተርሚናል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጥበቃ እና ጽዳት አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መጫረት የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡
- 1. በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያሳይ መረጃ (Tax Clearance)፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው
- 2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ ከ500,000.00 ያልበለጠ በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ “የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት” በሚል ስም በማሰራት ከጨረታ ፖስታው ጋር በማቅረብ መጫረት ይችላሉ፡፡
- 3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ የሚመልሰው በድርጅቱ ድህረ ገጽ (www.eslse.et) በERP System Link:- Link በዋና መ/ቤት ምዝገባ ካካሄዱ በኋላ ብቻ (ከዚህ ቀደም ያልተመዘገቡ ከሆነ) በሚሰጣቸው መለያ ቁጥር መሠረት የሚሞሉ መሆኑን እናሳውቃለን::
- 4. የጨረታው መክፈቻ እና መዝጊያ ጊዜ ሲስተሙ ላይ በሚወጣው ቀን እና ሰዓት ይሆናል፡፡
- 5. ሲስተሙ ጨረታውን ከዘጋ በኋላ የሚመጣ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- 6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት
ወረታ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት
ደቡብ ጎንደር (ወረታ)