የሐራጅ ጨረታ ቁጥር ሐጅ/05/2018
በጅቡቲ የባህር ወደብ ላይ የቆይታ ጊዜያቸው ያለፈ እና ወደ ኢትዮጲያ የተላኩ ዕቃዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በአስመጪዎቻቸው ጥቅም ላይ የሚውሉበትን ወይም የሚወገዱበት አኳኋን ለመወሰን በወጣው መመሪያ ቁጥር 33/2005 ተራ ቁጥር 4.7 ላይ እንደተመለከተው በጅቡቲ የባህር ወደብ ላይ የቆይታ ጊዜቸው ያለፈ ዕቃዎች ከጅቡቲ ወደብ ተጓጉዘው በኢትዮጲያ የጉምሩክ ክልል ወደሚገኙ ደረቅ ወደቦች ወይም ሌሎች አመቺ የማከማቻ ሥፍራዎች ከደረሱበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አስመጪዎች በዕቃዎቹ ላይ ሊከፈል የሚገባውን ቀረጥና ታክስ፤የወደብ አገልግሎት ክፍያ እንዲሁም ዕቃውን ከጅቡቲ ወደብ ለማጓጓዝ እና በደረቅ ወደቦች ወይም በሌሎች አመቺ የማከማቻ ሥፍራዎች እንዲቆዩ ለማድረግ የወጣውን ማንኛውንም ወጪ ከፍለው ዕቃዎችን እንዲረከቡ እንደሚያደርግ ነገር ግን አስመጪዎች በተሰጣቸው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚፈለግባቸውን ክፍያ ከፍለው ዕቃውን ካላነሱ እንደተተወ ዕቃዎች ተቆጥረው በሐራጅ የሽያጭ ዘዴ እንደሚሸጡ እና ሽያጩን ወይም የማስወገድ ሥራውን እንዲያከናውን ለድርጅታችን የኢትዮጲያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲከስ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ወቷል፡፡
ለዠርዝር መረጃ እዚህ ጋር ይጫኑ
Click Here