ያገለገሉ የኬ ስፓን ሼድ (K SPAN SHADE) እና ያገለገሉ እና የተጎዱ ኮንቴይነሮችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር DIS 01/2018
በድርጅታችን በቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ቅርንጫፍ እየተከናወነ ካለው የወደብ መሰረተልማት ሥራ ጋር ተያይዞ ፈርሰው የተቀመጡ ኬ ስፓን ሼድ (K SPAN SHADE) እና በድርጅታችን በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ጉዳት የደረሰባቸውን 5 ባለ አርባ ጫማ እና 13 ባለ 20 ጫማ በድምሩ 18 የተጎዱ ኮንቴይነሮችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በግልፅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ድርጅት/ግለሰብ በድርጅታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ለመጀመሪያ ቀን ከወጣበት ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 8 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማለትም ከማክሰኞ ጥቅምት 25 እስከ ሰኞ ህዳር 1 ቀን 2018ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30ሰዓት እና ከሰዓት ከ7፡30ሰዓት እስከ 11፡30 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30ሰዓት እንዲሁም ጨረታው እስከሚታሽግበት ማክሰኞ ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30ሰዓት እና ከሰዓት ከ7፡30ሰዓት እስከ ከ8፡00 ሰዓት በፊት የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ/ በመክፈል ለገሃር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት እና የገዙበትን ማስረጃ በመያዝ ፈርሰው የተቀመጡ ኬ ስፓን ሼድ (K SPAN SHADE) በቃሊቲ ወደብና ተርሚናል እንዲሁም የተጎዱ ኮንቴይነሮችን በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ከላይ ለሰነድ ሽያጭ በተቀመጠው ቀን እና ሰዓት መሰረት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ማክሰኞ ህዳር 2 ቀን 2018ዓ.ም ከሰዓት 8፡00ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ሰነድ የገዙ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን በፖስታ ውስጥ በማሸግ እስከ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመከፈት አይታገድም፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115549257/0951414204 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ