እንኳን ለ1446ኛው ኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ

በሀገራችንና እና በውጭ ሀገር በተለያዩ የስራ መስክ ላይ ተሰማርታችሁ ሀገራችሁን በባሕር ትራንስፖርት፣ በየብስ ትራንስፖርት፣ በተለያዩ ወደቦች እና በዋና መ/ቤት አዲስ አበባ ውስጥ እያገለገላችሁ የምትገኙ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ እስልምና እምነት ተከታይ አመራሮችና ሰራተኞቻችን፣ ክቡራን ወኪሎቻችን፣ ደንበኞቻችን እና ለመላ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ1446ኛው ኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። የአረፋ በዓል ከኃይማኖታዊ ትውፊቱ ባሻገር መተሳሰብ የሚጎላበት፣ አብሮነት የሚፀናበት፣ ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት፣ ርህራሄ የሚነግስበት የሰላም በዓል እንደሆነ ይታወቃል:: በዓለም ደረጃ የምንታወቅበትን ይህን ኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነታችንን በዓለት ላይ በማጽናት አይቀሬውን የኢትዮጵያን ልዕልና ለማረጋገጥ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንነሳ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ :: በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ!
መልካም በዓል፣ ኢድ ሙባረክ !
በሪሶ አመሎ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ