Happy Meskel Festival for all ESL Customers and Employees

በሀገራችንና እና በውጭ ሀገራት ኢባትሎ በሚሰራባቸው የስራ መስኮች ላይ ተሰማርታችሁ ሀገራችሁን በባሕር ትራንስፖርት፣ በየብስ ትራንስፖርት፣ በጅቡቲ ኤም ቲ ኤስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ በተለያዩ ወደቦች፣ በዋና መ/ቤት እና በሁሉም ቅርንጫፎቻችን እያገለገላችሁ የምትገኙ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የክርስትና እምነት ተከታይ ሰራተኞቻችን፣ ክቡራን ወኪሎቻችን፣ ደንበኞቻችን እና ለመላ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ 2017 ዓ.ም የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነታችንን ከመቼውም ጊዜ በላይ በማጠናከር ለውጤታማነት እንድንተጋ እና የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንነሳ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ :: በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር እና የብልጽግና እንዲሆንልን እመኛለሁ!
ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን ፈጣሪ ይባርክ!
መልካም የመስቀል በዓል ! በሪሶ አመሎ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ
መልካም በዓል