በባህር ትራንስፖርት ማጓጓዣ ዋጋ ላይ የተደረገ ማሻሻያ

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ብሎም በሀገራችን የተከሰተውን የኖቭል ኮሮና ቫይረስ (Covid-19) ወረርሽኝ ተከትሎ እየተቀዛቀዘ የመጣውን የንግድ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት የሚያግዝ በባህር ትራንስፖርት ማጓጓዣ ዋጋ ላይ ከአሁን ቀደም ለደንበኞች ከሚያቀርበው አገልግሎት ላይ እ.ኤ.አ ከጁን 1 ቀን 2020 ጀምሮ ቅናሽ ማድረጉን ሲገልጽ በደስታ ነው፡፡ በዚህም፡- • በአውሮፓና አፍሪካ የንግድ መስመሮች በሚገኙ 103 ወደቦች ባለ 20 ጫማ ኮንቴይነር ላይ የ9.31% እንዲሁም 60 ወደቦች እስከ 26.59% የሚደርስ ቅናሽ ሲደረግ ባለ 40 ጫማ ኮንቴይነር ላይ ደግሞ 85 ወደቦች 10.67% እንዲሁም 79 ወደቦች ላይ እስከ 28.02% የሚደርስ ቅናሽ ተደርጓል፡፡ • በሩቅ ምስራቅና ቻይና የንግድ መስመሮች በሚገኙ 41 ወደቦች ባለ 20 ጫማ ኮንቴይነር ላይ የ9.31% እንዲሁም 75 ወደቦች እስከ 26.59% የሚደርስ ቅናሽ ሲደረግ ባለ 40 ጫማ ኮንቴይነር ላይ ደግሞ 55 ወደቦች 10.67% እንዲሁም 63 ወደቦች ላይ እስከ 28.02% የሚደርስ ቅናሽ ተደርጓል፡፡ • በመካከለኛው ምስራቅና ህንድ የንግድ መስመሮች በሚገኙ 11 ወደቦች ባለ 20 ጫማ ኮንቴይነር ላይ የ9.31% እንዲሁም 23 ወደቦች እስከ 26.59% የሚደርስ ቅናሽ ሲደረግ ባለ 40 ጫማ ኮንቴይነር ላይ ደግሞ 16 ወደቦች 10.67% እንዲሁም 18 ወደቦች ላይ እስከ 28.02% የሚደርስ ቅናሽ ተደርጓል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥቅል እቃና ብረትን ለሚያስመጡ ደንበኞች በሁሉም የንግድ መስመሮች ላይ የ10% ቅናሽ ማድረጋችንን ለክቡራን ደንበኞቻችን እናስታውቃለን፡፡ ለጥረትዎ እሴት እንጨምራለን! የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት