ለአስመጪ ደንበኞቻችን በሙሉ፡-

አንዳንድ አስመጪዎች ከውጭ ሐገር በኮንቴይነር ተጓጉዞ የመጣ ዕቃን ከተረከባችሁ በኋላ ዕቃውን ማስቀመጫ ቦታ ተቸገርን በማለት ያስመጣችሁበትን ኮንቴይነር ገዝተን እናስቀር የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ ለድርጅታችን እያቀረባችሁ ትገኛላችሁ፡፡ ሆኖም እነዚህ ኮንቴይነሮች አገልግሎት ለመስጠት በኪራይ ላይ ያሉና በዋስትና የመጡ በመሆናቸው ከውጭ ምንዛሬ አጠቃቀምና ከጉምሩክ ፎርማሊቲ አፈፃፀም አኳያ ችግር እያጋጠመን ይገኛል፡፡ በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ዕቃ ይዘው ከውጭ የገቡ እና የሚገቡ ኮንቴይነሮችን የሽያጭ ጥያቄ የማንቀበል መሆኑን እየገለጽን፣ ኮንቴይነሩ ዕቃውን እንደያዘ እንዲቆይ የምትፈልጉ አስመጪዎች በማስጫኛ ወደብ ላይ በራሳችሁ ኮንቴይነር እንድትጭኑ እያሳሰብን፣ ኮንቴይነሩ የግላችሁ መሆኑን ለማሳየት በሰነዶች ላይ ‘Shipper own container-SOC’ የሚል ሐረግ በማስገባት ማጓጓዝ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ለጥረትዎ ዕሴት እንጨምራለን! የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት