Beyond the Sea.

Ethiopian Shipping and Logistics

የተወረሱ ንብረቶች የሐራጅ ሽያጭ ጨረታ ማከናወኛ ጊዜ ማራዘሚያ ማስታወቂያ

በጅቡቲ የባህር ወደብ ላይ የቆይታ ጊዜያቸው ያለፈ እና ወደ ኢትዮጲያ የተላኩ ዕቃዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በአስመጪዎቻቸው ጥቅም ላይ የሚውሉበትን ወይም የሚወገዱበት አኳኋን ለመወሰን በወጣው መመሪያ ቁጥር 33/2005 ተራ ቁጥር 4.7 ላይ እንደተመለከተው በጅቡቲ የባህር ወደብ ላይ የቆይታ ጊዜቸው ያለፈ ዕቃዎች ከጅቡቲ ወደብ ተጓጉዘው በኢትዮጲያ የጉምሩክ ክልል ወደሚገኙ ደረቅ ወደቦች ወይም ሌሎች አመቺ የማከማቻ ሥፍራዎች ከደረሱበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አስመጪዎች በዕቃዎቹ ላይ ሊከፈል የሚገባውን ቀረጥና ታክስ፤የወደብ አገልግሎት ክፍያ እንዲሁም ዕቃውን ከጅቡቲ ወደብ ለማጓጓዝ እና በደረቅ ወደቦች ወይም በሌሎች አመቺ የማከማቻ ሥፍራዎች እንዲቆዩ ለማድረግ የወጣውን ማንኛውንም ወጪ ከፍለው ዕቃዎችን እንዲረከቡ እንደሚያደርግ ነገር ግን አስመጪዎች በተሰጣቸው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚፈለግባቸውን ክፍያ ከፍለው ዕቃውን ካላነሱ እንደተተወ ዕቃዎች ተቆጥረው በሐራጅ የሽያጭ ዘዴ እንደሚሸጡ እና ሽያጩን ወይም የማስወገድ ሥራውን እንዲያከናውን ለድርጅታችን የኢትዮጲያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲከስ አገልግሎት ድርጅት በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሞጆ ወደብና ተርሚናል እና በቃሊቲ ገላን ያሉ ንብረቶችን በሐራጅ ሽያጭ ለመሸጥ ታህሳስ 24 ቀን 2017ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው ማስታወቂያ የጉብኝትና C.P.O ማስገቢያ ቀን ጥር 6 ቀን 2017ዓ.ም አብቅቶ ጨረታው ጥር 8 ቀን 2017ዓ.ም እንደሚከናወን የተቀመጠ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች የሐራጅ ጨረታው ከታች በተመለከተው የጊዜ መርሃግብር መሰረት ተራዝሟል፡፡

በሞጆ ወደብና ተርሚናል የሚገኙ ንብረቶች የናሙና ዕይታ እና C.P.O ማስገቢያ ቀንና ሰዓት

የዕቃው ዓይነት የናሙና ዕይታ እና C.P.O ማስገቢያ ቀንና ሰዓት የሐራጅ ጨረታው የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት
የተለያዩ አይነት ንብረቶች፤ጀነሬተሮች እና ተሽከርካሪዎች ቅዳሜ፤እሁድን እና በአላትን ሳይጨምር እስከ ጥር 12 ቀን 2017ዓ.ም ጠዋት ከ3፡00-6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት ከ8፡00- 11፡00 ሰዓት ብቻ
  • የሐራጅ ጨረታው የሚከናወንበት ቀን እረቡ ጥር 14/2017 ዓ.ም ጨረታው የሚጀመርበት ሰዓት
  • ጠዋት ከ3፡00-6፡00 ሰዓት ካላለቀ ከሰዓት ከ8፡00-12፡00 ሰዓት
ጥብቅ ማሳሰቢያ፡- የናሙና ዕይታ እና C.P.O ማስገቢያ ከላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት ብቻ በዋናው መስሪያቤት የምናስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

በቃሊቲ ገላን የሚገኙ ንብረቶች የናሙና ዕይታ እና C.P.O ማስገቢያ ቀንና ሰዓት


የዕቃው ዓይነት የናሙና ዕይታ እና C.P.O ማስገቢያ ቀንና ሰዓት የሐራጅ ጨረታው የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት
የተለያዩ አይነት ንብረቶች፤ጀነሬተሮች እና ተሽከርካሪዎች ቅዳሜ፤እሁድን እና በአላትን ሳይጨምር እስከ ጥር 14 ቀን 2017ዓ.ም ጠዋት ከ3፡00-6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት ከ8፡00- 11፡00 ሰዓት ብቻ
  • የሐራጅ ጨረታው የሚከናወንበት ቀን አርብ ጥር 16/2017 ዓ.ምጨረታው የሚጀመርበት ሰዓት
  • ጠዋት ከ3፡00-6፡00 ሰዓት ካላለቀ ከሰዓት ከ8፡00-12፡00 ሰዓት
ጥብቅ ማሳሰቢያ፡- የናሙና ዕይታ እና C.P.O ማስገቢያ ከላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት ብቻ በዋናው መስሪያቤት የምናስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0115549257/0115549478/0951414204 መደወልና መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት